አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

የፕሮጀክት ምልከታ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶር) በስልጤ ዞን በአለም ገበያ ከተማ የአለሜ መዝናኛ ፓርክን ተመለከቱ

የፕሮጀክት ምርቃ

በስልጤ ዞን በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡና የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

የከተማችን ከፊል ገፅታ!

በፈጣን ዕድገትና የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የምትገኘው፣ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመቻቻል መናገሻዋ የአላምገበያ ከተማ አስተዳደር።

የፕሮጀክቶች ምልከታ

አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ምልከታ ተደረግ

የዳሎቻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አልዬ ፈረጆ መልዕክት

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ውብ ተምሳሌት የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። የተለያዩ ማንነቶች፣ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች በአንድነት የደመቁባት ሀገራችን፣ ልዩነቷን ወደ ጥንካሬና ውበት በመቀየር ለዘመናት በመከባበርና በመቻቻል የኖረች ናት። ዜጎቿም ውድ ሕይወታቸውን በመስዋዕትነት በመክፈል የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረው ለትውልድ አስረክበዋል።

ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠሩ የተዛቡ ትረካዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች ይህንን የጋራ እውነታችንን ለመሸርሸር ሞክረዋል። አንዳንድ ኃይሎችም አባቶቻችን የሀገር ምሰሶ ያደረጓቸውን እሴቶች የጥንካሬ ምንጭ ሳይሆን የድክመት ምንጭ ለማድረግ ሲሰሩ ቆይተዋል።የሀገራዊ ለውጡ ፈንጣቂ የሆነው የብልፅግና ፓርቲ ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በዘላቂነት መፈወስ የሚቻለው በአገራዊ አንድነት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። ለዚህም ነው አገራዊ አንድነታችንን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ የትኩረታችን ማዕከል ያደረግነው።

 በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ ዳሎቻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በወረዳዋ ነዋሪዎች የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።ዳሎቻ ወረዳ የስልጤ ሕዝብ  የሰላም፣ የአንድነትና የልማት ማዕከል እንደመሆኗ፣ በተለያዩ ዘርፎች የሚመዘገቡ ውጤቶች የወረዳዋን ብሎም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የሚያበረክቱ ናቸው። ባለፉት ዓመታት ዳሎቻ ወረዳ የሰላምና የመረጋጋት አየር በማጠናከር፣ የወረዳ ልማትን በማስፋፋት፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማሳደግ እንዲሁም የሕዝብና የመንግስት ትስስርን በማጠናከር የሚታዩ ውጤቶችን አስመዝግበናል። የዳሎቻ ወረዳ የብልፅግና አሻራም በተጨባጭ እየጎላ መጥቷል። እርግጥ ነው፣ በጉዟችን ላይ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ሆኖም እኛ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ፣ አቅማችንን ወደ ላቀ ውጤት፣ ተግዳሮቶችንም ወደ ታላቅ ስኬት በመቀየር፣ በመተሳሰብና በወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ውድ የሆነችውን ዳሎቻ ወረዳን፣ የስልጤን ሕዝብና ታላቋን ኢትዮጵያ ከፍ ለማድረግ በፅናት ወደፊት ተጉዘናል፤ ጉዟችንንም እንቀጥላለን! በዳሎቻ ወረዳ በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መላው የወረዳችን ማህበረሰብ፤ የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር፣ ድህነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ሙስናን በቆራጥነት በመታገል፣ የድካማችን ማማና የልፋታችን ውጤት የሆነውን ሁሉን አቀፍ ብልፅግና ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ትጋትና በተቀናጀ ተሳትፎ ነው። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የዳሎቻ ወረዳ ነዋሪዎች እንደ ሁልጊዜው የጽናታችን አለኝታና የጉዟችን ደጋፊ ሆናችሁ ከጎናችን እንደምትቆሙ ሙሉ እምነት አለን። በመጨረሻም፣ ለዴሞክራሲያችን መጎልበት የማይተካ ሚና ያላችሁ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለዳሎቻ ወረዳ፣ ለስልጤ ሕዝብና ለታላቋ ኢትዮጵያ ብልፅግና ሲባል በትብብርና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ። 

                                                                                      ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ ፍቅርና ልፋት ትበለፅጋለች!

                                                                                                            አመሰግናለሁ!"

አምልጦዎት ይሆን |You May Have Missed

      

ሚዲያ እና ገጽ| Our Media

አጋሮቻችን I Our Partner