በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የተመራ የኢንስፔክሽን ቡድን በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የፈፃሚ ማዘጋጃ  የዕቅድ ዝግጅት ላይ ድጋፍና ክትትል  መካሄድ ጀመረ።
በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የተመራ የኢንስፔክሽን ቡድን በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የፈፃሚ ማዘጋጃ የዕቅድ ዝግጅት ላይ ድጋፍና ክትትል መካሄድ ጀመረ።
መስከረም ፣20/2019(የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን )
በስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኢንስፔክሽን ቡድን በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የፈጻሚ ማዘጋጃ የዕቅድ ዝግጅት ሂደት ለመደገፍና ለመከታተል የኢንስፔክሽን ሥራ መካሄድ ጀምሯል።
የድጋፍና ክትትል ሥራውን የሚያከናውነው ቡድን በዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳሊያ ሀሰን፣ የዲሞክራሲና ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማን ከድር እና የስልጤ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መህቡባ ሱራጅ የተመራ ነው።
ይህ የኢንስፔክሽን ቡድን በፈፃሚ ማዘጋጃዉ አሁን ባለበት የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ጠንካራ ጎኖችንና ክፍተቶችን በመለየት አፈጻጸሙን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ግብረ-መልስ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።